የF-1 ተማሪነት ስታተስን ጠብቆ ማቆየት
- getachewmulu28
- Jun 1
- 2 min read

የF-1 ተማሪነት ስታተስን ጠብቆ ማቆየት
ክፍል ሦስት
በMulu Law Group ለኢትዮጵያ የF-1 ቪዛ ላላቸውተማሪዎች እንዲረዳ የተዘጋጀ።
ረ) እንደ F-1 ተማሪ ሆኖ ከአሜሪካ ውጪ መጓዝ፤
• ዓለም አቀፍ የጉዞ ዕቅዶችን ከማድረግዎ በፊት፣ የSEVIS መዝገባዎ ወቅታዊ እና በ"Active" (በሥራ ላይ) ሁኔታ ላይመሆኑን ያረጋግጡ። DSO (የተማሪዎች ጉዳይ ኃላፊ) በI-20 Form ላይ “የጉዞ ማረጋገጫ” በሚለው ክፍል ውስጥባለፈው ዓመት ውስጥ መፈረሙን እና ከአምስት ወር በላይከሀገር እንደማይወጡ ያረጋግጡ። በመጠባበቅ ላይ ያለየተግባር ስልጠና ማመልከቻ ካለዎት፣ ከዩናይትድ ስቴትስመውጣት አይመከርም።
• USCIS የOPT ማመልከቻዎን ካጸደቀ፣ የሥራ ፈቃድ ሰነድ(EAD) በአሜሪካ አድራሻዎ ይደርስዎታል። ወደ ዩናይትድስቴትስ ለመግባት EAD በእጅዎ ሊኖርዎት ይጠበቃል።
• ወደ አሜሪካ የአየር ወይም የባህር በር ሲደርሱ፣ የአሜሪካየጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ (CBP) መኮንኖችንለመጀመሪያ እና አንዳንዴም ለሁለተኛ ምርመራ ያገኛሉ።የCBP መኮንን እንደሁኔታው የሚሰራ ፓስፖርትዎን፣ የI-20 Form፣ የተማሪ ቪዛዎን እና የተግባር ስልጠና የሥራ ፈቃድሰነድዎን (EAD) ሊጠይቅ ይችላል። የCBP መኮንኖች የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችዎን ሊፈትሹ ይችላሉ።
ሰ) የF-2 ጥገኞች
• የF-2 ጥገኞች በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ ህጋዊ ደረጃቸውን ጠብቀው መኖር አለባቸው። የF-2 ጥገኞች በተወሰኑ ፕሮግራሞች የትርፍ ጊዜ ትምህርት መከታተል ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የF-2 ጥገኞች መሥራት አይፈቀድላቸውም።
ሸ) የአድራሻ ለውጥን ሪፖርት ያድርጉ
• የSEVIS መዝገባዎ እንዲዘመን/Update እንዲሆን የአድራሻለውጥ ከተደረገ በ10 ቀናት ውስጥ ለተማሪ ጉዳዮች ኃላፊ(Designated School Official) እና ለዩናይትድ ስቴትስዜግነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎት (United States Citizenship and Immigration Services) ያሳውቁ።
ቀ) የF-1 ደረጃ ማጣት
• የኢሚግሬሽን ደንቦችን ወይም የአሜሪካን ህጎች ከጣሱ፣የF-1 ደረጃዎን እና ጥቅማ ጥቅሞችዎን (ለምሳሌ የስራፈቃድ) ሊያጡ ይችላሉ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርበአሜሪካ ውስጥ እያሉ በተለያዩ ምክንያቶች ቪዛዎንሊሰርዝ ይችላል። ቪዛ መሰረዙ በራሱ ከህጋዊ ደረጃአያስወጣዎትም። የSEVIS መዝገባዎ በDSO (የተማሪዎችጉዳይ ኃላፊ) ወይም በICE (የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክማስፈጸሚያ) ሊቋረጥ ይችላል። ቪዛዎ ከተሰረዘ ወይምየSEVIS መዝገብዎ ከተቋረጠ፣ ከሀገር የማስወጣት እና/ወይም የማቆያ እርምጃ ሊወሰድብዎ ስለሚችል የታመነጠበቃ ምክር ማግኘት አለብዎት።
ጠበቃውን ለመገናኘት በዝግጅት ላይ ሳሉ የሚከተሉትንማድረግ አለብዎት፡- የሚመለከተውን የኢሚግሬሽን ታሪክበሙሉ አውርደው ይመዝግቡ፣
የሚከተሉትን ጨምሮ፡-
• የSEVIS መዝገብ እና ሁሉም የI-20 Form እናማስታወሻዎች፤
• የI-94 እና የጉዞ ታሪክ፤
• የፓስፖርትዎን፣ የቪዛዎችዎን፣ የሁሉም የI-20 ቅጾችዎን እናየሁለቱንም የEAD ጎኖች ዲጂታል ቅጂዎች ያስቀምጡ፤
• መረጃ ለሶስተኛ ወገን እንዲለቀቅ ለማስቻል Family Educational Rights and Privacy Act (FERPA) እና የICE Privacy Waiver (Form 60-001) ይፈርሙ



Comments