የF-1 ተማሪነት ስታተስን ጠብቆ ማቆየት
- getachewmulu28
- Jun 1
- 1 min read

Part -one
በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንደ F-1 ዓለም አቀፍ ተማሪ የኢሚግሬሽን ስታተስዎን ጠብቆ ማቆየት የእርስዎ ኃላፊነትነው። በህጉ መሰረት ለመቆየት እና ትምህርትዎን ወይም ህጋዊ ቆይታዎን አደጋ ላይ ላለመጣል እነዚህን ቁልፍመመሪያዎች ይከተሉ፡
ክፍል አንድ
በMulu Law Group ለኢትዮጵያ የF-1 ቪዛ ላላቸውተማሪዎች እንዲረዳ የተዘጋጀ።
ሀ) አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ጠብቆ ማቆየት፤
የF-1 ተማሪዎች የሚከተሉት ሰነዶች ሊኖሯቸው ይገባል፡-
1. የI-20 Form፤
2. ወደፊት ቢያንስ ለ6 ወራት የሚሰራ ፓስፖርት። ፓስፖርቱ ጊዜው ከማለፉ በፊት በተማሪው በራሱ በኩልበኤምባሲው እንዲታደስ ማድረግ የተማሪው ኃላፊነት ነው።
ለ) I-94 መዝገብ “D/S” እና “F-1” ደረጃን የሚያሳይ፤
D/S ማለት “የቆይታ ጊዜ” (Duration of Status) ማለት ነው፡፡ በI-94 ላይ የተወሰነ የመጨረሻ ቀን የለም። D/S በI-20 Formላይ እንደተገለጸው የሙሉ ጊዜ የትምህርት መርሃ ግብርን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ጊዜ፣ እንዲሁም ማንኛውንምየተፈቀደ የተግባር ስልጠና ጊዜ እና የቪዛዎን ሁኔታ ወደ ሌላ ለመቀየር ወይም ከዩናይትድ ስቴትስ ለመውጣት የ60 ቀናትየgrace periodን ያካትታል።
ሐ) የትምህርት መስፈርቶች፤
1) በI-20 Form ላይ በተዘረዘረው ትምህርት ቤት መከታተል፤ የF-1 የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የሙሉ ጊዜትምህርት መውሰድ እና በየሴሚስተሩ ቢያንስ 12 ክሬዲት ሰዓታት መመዝገብ አለባቸው።
2) በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ያሉ ደግሞ ቢያንስ ለዘጠኝ ክሬዲት ሰዓታት መውሰድ አለባቸው፤
3) በአንድ ሴሚስተር የonline ትምህርት (ሶስት ክሬዲት ሰዓታት) ብቻ የሙሉ ጊዜ ምዝገባ አካል ሆኖ ሊቆጠርይችላል።
4) የሙሉ ጊዜ ትምህርት የማይወስዱ ከሆነ፣ ከሚያስፈልገው የክሬዲት ሰዓት በታች ከመውረድዎ በፊት ከአማካሪዎየጽሑፍ ፈቃድ ማግኘት አለብዎት፤ በትምህርት ቤትዎ እንደተገለጸው ጥሩ የትምህርት ደረጃን ጠብቆ ማቆየትአለብዎት።
መ) የፕሮግራም መሻሻሎች እና ለውጦች፤
· የI-20 Form ወቅታዊ ያድርጉ። የሚከተሉትን ለውጦች ከተከሰቱ በ10 ቀናት ውስጥ ለDSO (የተማሪዎች ጉዳይኃላፊ) ያሳውቁ
· የትምህርት ክፍል፣ የዲግሪ ደረጃ ወይም የገንዘብ ምንጭ ለውጥ፤ የአድራሻ ወይም የስልክ ቁጥር ለውጥ፤ የስምለውጥ ፤ፕሮግራምዎን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜ ከፈለጉ የI-20ዎን ጊዜ ከማለፉ በፊት ያራዝሙ። ክፍል ሁለት ይቀጥላል።



Comments